የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በእርስ ቁጥጥር በኢትዮጵያ የፖሊሲ እና የሕግ ማዕቀፍ አጭር ማብራሪያ

የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በእርስ ቁጥጥር በኢትዮጵያ የፖሊሲ እና የሕግ ማዕቀፍ አጭር ማብራሪያ ሰነድ በመርሳ ሚዲያ ኢንስቲትዩት ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው፡፡ ይህ አጭር ማብራሪያ የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በእርስ ቁጥጥር ሥርአት ፅንሰ ሀሳብን፣ በአገራችን በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ውስጥ እና በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት መካከል  የሚከናወነውን የእርስ በእርስ ቁጥጥር ሥርዓት ለማጠናከር የተደነገጉ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፎችን፣ ተግባራዊ አፈፃፀማቸውን እንዲሁም የአገራት ልምዶችን አካቶ ተዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም ይህ ሰነድ ለጋዜጠኞች እና ለሚዲያ ባለሙያዎች ስለ እርስ በእርስ ቁጥጥር ያላቸውን ግንዛቤ እና ክህሎት የሚያሰፉበት፣ የሚዲያ ተቋማት ስለ እርስ በእርስ ቁጥጥር  ለሰራተኞቻቸው የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጡበት፣ የኢዲቶሪያል ፖሊሲያቸውን የሚፈትሹበት እና የሚያጠናክሩበት፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጋዜጠኝነት እና የሥነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህራን ለማስተማሪያነት  እንዲሁም ተማሪዎች ለመማሪያ እና የዕውቀት አድማሳቸውን ለማስፋት እንዲጠቀሙበት ታስቦ የተዘጋጅ ማብራሪያ ሰነድ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *