ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሃቅን ለማጣራት እንዲችሉ የሚያግዝ ማጣቀሻ

የሃሰተኛ መረጃ እና ሃሰተኛ ዜናዎች ስርጭት በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ የበርካታ አካላትን ትኩረት ከሳበ ዓመታት ተቆጥረዋል። አንዳንድ አካላት ሃሰተኛ መረጃዎች ከሚያስከትሉት መዘዝ አንጻር ሃሰተኛ መረጃዎችን የመረጃ ወረርሽኝ እያሉ መጥራትን ይመርጣሉ፤ ሰላም እንዲደፈርስ ከማድረግ አንጻር፣ በብሄሮችና በተለያዩ እምነት ተካታዮች መካከል ግጭቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ በአጠቃላይ በህዝቦች ሰላማዊ ኑሮ ላይ ችግሮችን እየፈጠሩ ስለሚገኙ። ሃሰተኛ መረጃዎች ከሚያስከትሉት ጉዳት አንጻር የቅድመ-መከላከያ ስራዎችን መስራት አስፈላጊ በመሆኑ የመገናኛ ብዙሃን፣ የቴክኖሎጂ ተቋማት፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አዋጭ ነው የሚሉትን እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ። በኢትዮጵያም የጥላቻ ንግግርን እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዋጅ መውጣቱ ይታወሳል። አዋጁ በአንድ በኩል የአገር ሰላምና የሕዝቦችን ደህንነት ከማስጠበቅ አንጻር የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚወሰዱት እርምጃዎች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በአንጻሩ ደግሞ በትክክል ካልተተገበረ የመናገር ነጻነት ላይ ጥላ ሊያጠላ ይችላል። የተቀናጀ የመከላከል ስራ መስራት የጥላቻ ንግግር እና ሃሰተኛ መረጃ የሚያስከትሉትን አሉታዊ ጫና ለመቀነስ ይረዳል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *