Fact-checking Module
ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሃቅን ለማጣራት እንዲችሉ የሚያግዝ ማጣቀሻ የሃሰተኛ መረጃ እና ሃሰተኛ ዜናዎች ስርጭት በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ የበርካታ አካላትን ትኩረት ከሳበ ዓመታት ተቆጥረዋል። አንዳንድ አካላት ሃሰተኛ መረጃዎች ከሚያስከትሉት መዘዝ አንጻር ሃሰተኛ መረጃዎችን የመረጃ ወረርሽኝ እያሉ መጥራትን ይመርጣሉ፤ ሰላም እንዲደፈርስ ከማድረግ አንጻር፣ በብሄሮችና በተለያዩ እምነት ተካታዮች መካከል ግጭቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ በአጠቃላይ በህዝቦች ሰላማዊ ኑሮ ላይ ችግሮችን እየፈጠሩ ስለሚገኙ። ሃሰተኛ መረጃዎች ከሚያስከትሉት …